ምክር ቤት የምሕረት አዋጁን አጸደቀ

የተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ። በስብሰባውም ሲጠበቅ የነበረው እና በተለያየ የወንጀል ድርጊት ለተሳተፉ ሰዎች ምሕረት ለመስጠት የቀረበው ረቂቅ የምሕረት አዋጅ ፤ አዋጅ ቁጥር 1096ን አጽድቋል።…