የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ከፓርቲ አባልነት መውጣት አልያም ተቋሙን መልቀቅ አለባቸው ተባለ

የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆኑ ብሄራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ከፓርቲ አባልነት መውጣት አልያም ተቋሙን መልቀቅ አለባቸው– ጀነራል አደም መሀመድ

..
ተቋሙን ከፓለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ከማድረግ ባሻገር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰራበትና የሚሳተፍበት ይደረጋል።

መንግስት በተቋሙ ላይ አዲስ ሀገራዊ ሀላፊነት በመጠላሉ አለም አቀፋዊ የመረጃ ትስስርና ፍሰት ጋር እራሱን አዋህዶ መቀጠል አለበት።
….
ተቋሙ ኢትዮጵያዊነትን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማሻገር ዋና ተግባሩ እንዲሆን ይደረጋል።

ተቋሙ የሚፈራ ሳይሆን የሚወደድና የሚከበር እንዲሆን ይሰራል ያሉት ጀነራሉ ለዚህም አመራሮችና ባለሙያዎች ህግና ስርዓትን ተከትሎ እንዲሰሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።