ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾሙ።ሹመቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለረጅም በተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ምህሁር ናቸው።
ከዚህ ባሻገርም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሽግግር መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመታት ላይ ለአጭር ጊዜ የትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር አገልግለው የነበሩ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልም ነበሩ።
ፕሮፌሰሩ ኅብረትና መድረክን በመሳሰሉ የፓርቲዎች ስብስቦች እንዲፈጠሩ ጉልህ ሚና የነበራቸው ሲሆን ፓርቲዎቹን በአመራርነትም አገልግለዋል።
Image may contain: 1 person, sitting