ህግን ለማስከበር ጥፋተኛን በጥፋቱ ልክ የመጠየቅ ባህል መዳበር እንዳለበት ተሰማ

በአዲሱ አመት አሁን ያጋጠሙትን አገራዊ ፈተናዎች ለማለፍ አንድነትን ማጠናከር ይገባል…ፖለቲከኞች
(ኢዜአ) በአዲሱ አመት አሁን ያጋጠሙትን አገራዊ ፈተናዎች ለማለፍ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ገለጹ።
ለአዲስ ዓመት የ’እንኳን አደረሳችሁ’ መልዕክት ያስተላለፉት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አመራሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን አንድነት ለማጠናከር በመግባባት መስራት ያስፈልጋል።
የአዴፓ ሊቀመንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ ”2012 ዓ.ም ጥሩ እንቅስቃሴ የታየበትና ችግሮችን ለመፍታት ጥረት የተደረገበት ቢሆንም አዳዲስ ችግሮችም ተስተውለውበታል” ብለዋል።
የለውጥ ጉዞው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ ጽንፍ በያዘ የዘረኝነት አስተሳብ፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች የሚፈጠሩ ጫናዎች የተነሳ አዝጋሚ ሊሆን መቻሉን ገልጸዋል።
ህግን ለማስከበር ጥፋተኛን በጥፋቱ ልክ የመጠየቅ ባህል መዳበር እንዳለበት አመልክተዋል።
በ2012 ከተስተዋሉ መልካም ተሞክሮዎች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌትና የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብት ለማልማትና ለማስዋብ እየተሰራ ያለውን ስራ በአብነት አንስተዋል።