ጅማ አባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ

በዚህ ዓመት ፕርሚየር ሊጉን የተቀላቀሉት ጅማ አባጅፋሮች በሜዳቸው አዳማ ከተማን 5 ለባዶ በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነዋል። ከዚህ በተጨማሪም የፊት መስመር አጥቂያቸው ኦኪኪ አፎላቢ ዛሬ ያስቆጠራቸውን 4 ግቦች ጨምሮ በ23 ግብ የአመቱ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ጨርሷል።…