የናሽቪል ቴኔሲ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ ንብረት “ሸጦ ለመካፈል” የሚመስል እንቅስቃሴ ተጀመረ

በሽያጩ ላይ ዋና አቀንቃኞች አቶ ሳሙኤል ልዑል ሰገድና የሱ ተባባሪዎች (አብዛኛው የወያኔ ደጋፊዎች) የቤተክርስቲያኗን 214 Welch Road ላይ የሚገኘውን ንብረት ለመሸጥ ነው። በአሁኑ ሰዓት

  • 5 ኤከር የማያንስ መሬት ሲሆን በላዩ ላይ የሚከራዩ ቤቶችና የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን የነበረውን ጭምር ነው። (በወር  $5,000 ያህል እንደሚያገኝ ይገመታል)። ይህ ንብረት ሲከራይ የገንዘብ አሰባሰቡ ግልፅ አይደለም። ሌሎችም ችግሮች አሉ ወደፊት እንዘረዝራለን።
  • ይህንን “ሸጦ መካፈል” የሚመስለው እንቅስቃሴ በናሽቪል የሚገኙትን የኦርቶዶክስ አማኞች በሙሉ ማነጋገር ጀምሯል።  የደብረ ቀራንዮ መድሐኒዓለም የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ስለነበረ አሁን ከቤተክርስትያኑ በተለያየ ምክንያት የወጡና ሌላም ቤተክስርስቲያን የመሰረቱ እንደ ሐማረ ኖህ ኪዳነምሕረትና ደብረ ብርሀን ቅድስት ስላሴ  ቤተክርስቲያንና ሌሎችም አኩርፈው በየቤታቸው ያሉት ሁሉ ጉዳዩን መጠየቅና ጠበቃም ማነጋገር ጀምረዋል። ምንም እንኳን የቀድሞ አባሎች ተለይተው ቢወጡም አሁን ያለው ክፍፍል አንድ በሚሆንበት ጊዜ ንብረቱ የኦርቶዶክስ አማኙ ሁሉ መገልገያ እንደሚሆን ይገመታል። ነገር ግን ንብረት ሸጦ ለጥቂት ተፅኖ ለሚያደርጉ የወያኔ ደጋፊዎች ለማስረከብ የሚሯሯጡ በመገኘታቸው ሁሉንም እያነጋገረ ነው።

ዝርዝሩን ሰሞኑን ይዘን እንደምንቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።