ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለፍልሰታ ጾም በውይይት መድረክ ያደረጉት ቆይታ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እንዳመለከቱት የጾምና የሱባዔን ትርጉም ሳንረዳና ጠንቅቀን ሳናውቅ የምንጾም በሙሉ እንደዘንዶ ሱባዔ ሆነናል ይላሉ።የሰው ልጅ ጾምና ሱባኤ “ዘንዶው የበላውና የዋጠው ሲከብደው (hibernate) እንደሚያደርገው አይደለም ። ዘንዶው የበላው ተቃጥሎ እስኪያልቅ አይመገብም። ከዛም የበላው ሲያልቅና አዲስ ቆዳ ሲቀይር በአዲስ ጉልበት ሊበላና ሊውጥ እየተንቀለቀለ ለአደን ይሰማራል። እኛም ክርስቲያኖች ንስሐ ሳንገባ፣ የሐዋርያትን ምሳሌነት ሳናውቅ የምናደርገው ጾም ከዘንዶው ጾም አይለይም”። የሰው ልጆች ጾም ግን እንደዚህ አይደለም በማለት ቀሲስ አስተርአየ ከወንጌል እያመሳጠሩ በጥያቄና  መልስ በብስራተ ገብርኤል ቴሌቪዥን የሰጡትን ትምህርት አቅርበንላችኋል።