ከሲኖዶሳዊው ዕርቀ ሰላም ውይይት በፊት የተላለፈው ውግዘት እንዲነሣ የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ጠየቀ፤ “ልኡካኑ ሳይመጡ እንዲፈታ እንጠይቃለን”

በይቅርታ እና ምሕረት የኢትዮጵያ ትንሣኤ እየታየ ያለበት ወቅት ነው፤ የ20 ዓመት የኢትዮ-ኤርትራ ጠላትነት ሲፈታ ሲኖዶሱም አንድ ይኹን፤ ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላም ለታላቋ ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሊተገበር ይገባል፤ ባይሳካ፣የቤተ ክርስቲያን ችግር የበለጠ ይወሳሰባል፤ አገልግሎቷ ይጎዳል፤ የሊቃውንትና የካህናት ጸጋ፣የምእመናን ሞያና ገንዘብ ብክነት ይቀጥላል፤ “በአንድ እምነት ኹለት አስተዳደር” ሳቢያ ካህናት እየተጎዳን አንቀጥልም፤ የአገር ውስጥና የውጭ አመራር ብለን ሳንከፋፍል ለማገልገል እንገደዳለን፤ …

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE