እቅዳቸውን ለማክሸፍ የሚሞክረውን ሁሉ ጦርነት እንደሚገጥሙት ነግረውናል- ጉዳዩ ፖለቲካ ነው፤ የበላይነትን የመፍጠር የተረኝነት አባዜ ነው

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – መንግስትን ለሰላምና ለፍቅር እንዲበረታታ መደገፍ ማለት መንግስት በሕዝብ ላይ ተንኮል ሲያሴር እያዩ ዝም ማለት አይደለም። መተቸት ካለበት መታረም ካለበት ሽመልስ ብቻ ሳይሆን ፓርቲው ከነመሪው ነው። እቅዳቸውን ለማክሸፍ የሚሞክረውን ሁሉ ጦርነት እንደሚገጥሙት ነግረውናል።

የሽመልስ አብዲሳን ጉዳይ ሿሚው አካል አያውቅም ማለት ራስን ማታለል ነው። አብይ ይህን ጉድ አያውቅም ብሎ ለመታለል መሞከር ሞኝነት ነው። ጉዳዩ ፖለቲካ ነው፤ የበላይነትን የመፍጠር የተረኝነት አባዜ ነው። አብይ የኦሕዴድ ወይም የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ነው። አብይ የማያውቀው ሽመልስ የሚናገረው የተረኝነት ለውጥ ሂደት በፍጹም የለም።
ታከለም ሰራው ፤ሽመልስም ሰራው ፤ሌላው የኦሕዴድ አመራር ሰራው፤ አብይ በደንብ ያውቀዋል። ሽመልስን ከስልጣን ቢያባርሩትም ያሰቡትንና የነደፉትን ከመስራት ወደኃላ እንደማይሉ ኦሕዲዶች ራሳቸው እየነገሩን ነው። ደጋግመን ሰምተነዋል ይህንን እቅዳቸውን ለማክሸፍ የሚሞክረውን ሁሉ ጦርነት እንደሚገጥሙት ነግረውናል። እነ እስክንድር ነጋና የ አስራት ሚዲያ ሰዎችን የዚሁ ጦርነት ሰለባ ናቸው።
ብትወዱም ባትወዱም ቄሮን የፈጠረው ኦህዴድ ነው።ሰልፍ ስናስወጣም ስንበትንም የነበርን እኛ ነን። አምስት ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም፣ ለኦሮምኛ ብለን ነው።አዲስ አበባ ውስጥ በሕገወጥም ሆነ በህጋዊ መንገድ ሰው እናስገባለን። ብለውናል። እንግዲህ ሌላውን ለመደፍጠጥና የራስን ተረኝነት ለማበልጸግ ብቻ ሲባል ቋንቋዎች አመራረጥ ላይ ለሌላው አስቦ እንድልሆነ መናገር የሚያሳፍርና ከአንድ መሪ የማይጠበቅ ነው። አዲስ አበባንም የማትጠቅም ከተማ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነም ነግረውናል። የቄሮንም ወንጀል መሸከም የኦዴፓ ድርሻ ሊሆን ነው። ( https://mereja.com/video2/watch.php?vid=90ae85708 ) ብልጽግና መራሹ ኦሕዴድ እየሔደበት ያለው መንገድ ለሕዝብም ለሐገርም የማይጠቅምና ተረኝነትን ያዋሐደ መሆኑን በራሱ በባለስልጣኑ አንደበት መናገሩ አሳፋሪ ነገር ነው። #MinilikSalsawi