የደቡብ ሱዳኑ የተቃዋሚ መሪ ሪክ ማቻር የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታ ሊሰጣቸው ነው፡፡

የደቡብ ሱዳኑ የተቃዋሚ መሪ ሪክ ማቻር የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታ ሊሰጣቸው ነው፡፡

የደቡብ ሱዳን የተቀናቃኝ ኃይሎችን በማደራደር ላይ የምትገኘው የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አል ዴርዲሪ አህመድ እንደተናገሩት በአዲስ መልክ በሚዋቀረው የደቡብ ሱዳን መንግስት ውስጥ የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ወደ ኃላፈነታቸው ይመለሳሉ ብለዋል፡፡

የስልጣን ክፍፍሉ ከስምምነት የተደረሰው በትላንተናው ዕለት በኡጋንዳ ካምፓላ በተካሄደ ስን ስርዓት ላይ ነው፡፡
በአዲሱ የስልጣን ክፍፍል መርህ መሰረት ደቡብ ሱዳን የማቻርን ቦታ ጨምሮ የ4 ምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታ ይኖራታል፡፡
ይህም በአገሪቱ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲካሄድ የነበረውን ለእርስ በርስ ጦርነት መቋጫ ያመጣል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
በስምምነቱ ላይ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ተካፋይ ነበሩ፡፡
የአሁኑ ስምምነት ተቀናቃኞች ኢጋድ ባስቀመጠው አቅጥጫ ወደ ሰላም ካልተመለሱ አለም አቀፍ ማዕቀብ ሁሉ ሊጠብቃቸው እንደሚችል መጠበቁን ተከትሎ የተደረሰ ስምምነት ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ምንጭ፡ አልጀዚራ