ጎንደር፣ደብረታቦርና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ።

ጎንደር፣ደብረታቦርና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመርቀዋል፡፡

ደብረታቦር 3439 ተማሪዎችን በመደበኛና በኤክስቴንሽን መርሀ ግብር አስተምሮ አስመርቋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ 7ሺህ 187 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ82 ቅድመ ምረቃ በ 110 የሁለተኛ እና በ27 የሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በመደበኛው፣ በማታው እና በኤክስቴንሽን ወደ 50ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ10+3 ዲፕሎማ መርሀ-ግብር ዛሬ ከ2ሺህ በላይ መምህራንን አስመረቀ፡፡

ኮሌጁ በአዊኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ነው ሰልጣኝ መምህራኑን ያስመረቀው፡፡ የእንጅባራ መምህራን ኮሌጅ የዘንድሮ ተመራቂዎችን ጨምሮ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት ከ18ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃ መምህራንን አስመርቋል፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ2ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ዩኒቨርሲቲው ለኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡