ዝምባቡዌ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሸሽቶ የነበረን 850 ሚሊዮን ዶላር አስመለሰች᎓᎓

ዝምባቡዌ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሸሽቶ የነበረን 850 ሚሊዮን ዶላር አስመለሰች᎓᎓


የዝምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋዋ እንዳስታወቁት በህገወጥ መንገድ በተለያዩ አካላት ወጥቶ የነበረውን ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ተመልሷል፡፡

ፕሬዝዳንት ምናንጋዋ ሞሪታኒያ ላይ በተካሄደው በአፍሪካ ህብረት የፀረ ሙስና መድረክ ላይ ዝምባብዌ በህገወጥ መንገድ ከወጣው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ነው ተመላሽ የሆነው ገንዘብ ገቢ መደረጉን ያስታወቁት፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከሀገሪቱ ገንዘብ የወሰዱ አካላት የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ የሶስት ወራት ቀነ ገደብ መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ የተሰጠው ቀነ ገደብ ባለፈው መጋቢት ወር ተጠናቋል፡፡

ሙስናን በመታገል መንግስታት፣ የግል ዘርፍና ሲቪል ማህበራትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል ተብሏል፡፡

የ75 አመቱ ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ “በፕሬዝደንትነት ዘመኔ መንግስቴ በሙስና ትግል ቅድሚያ አድርጎ መስራት እንዳለበት፤ ለዚሁም የካቢኔ አባላት ሃብታቸውን የሚያሳውቁበት ልዩ የጸረ ሙስና ፍርድ ቤት አቋቁሜአለሁ” ማለታቸው ነው የተገለፀው ᎓᎓
ምንጭ፡ ሲጂቲኤን