የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ያደረጉት ውይይት አሁን ማምሻውን በድል ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ያደረጉት ውይይት አሁን ማምሻውን በድል ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ መጨረሻ ስድስት ዓላማዎችን የማሳካት ዓላማ ያለው ከኮሚቴው ሦስት፣ ከመጅሊስ ሦስት፣ ከገለልተኛ ወገን ሦስት በጥቅሉ ዘጠኝ አባላት ያሉት ዐዲስ ኮሚቴ ተዋቅረዋል፡፡

የዐዲሱ ኮሚቴ አባላትም አቡበክር አሕመድ፣ አሕመዲን ጀበል፣ ካሚል ሸምሱ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ኢድሪስ ሙሐመድ፣ ፕሮፌሰር ሙሐመድ ሐቢብ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍር፣ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን፣ ፈዲለተል ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ፣ ሸይኽ ኸድር ሑሰይን መሆናቸው ታውቋል፡፡ ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡