ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ እየተገደሉ፤ እየታፈኑ ያሉት የትግራይ ተወላጆች አይደሉም፤ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው::

« ከስልጣን በሰላም ወርዶ በሰላም እንዲኖር እድል የተሰጠው ህወሃት ብቻ ነው»አቶ ኦሃድ ቤናሚ – የሚዲያ አማካሪ
• ከ20 ዓመታት በላይ የመሩት የሱዳን፣ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ የሊቢያና የሌሎችም አረብ አገራት መሪዎች የተወገዱት በጦርነትና በአመፅ ነው::
Image may contain: one or more people and people sitting• በዚህ ቀጠና በሰላም የወረደው ህወሃት ብቻ ነው፤ በሰላም ወርዶ በሰላም እንዲኖር እድል የተሰጠው ህወሃት ብቻ ነው::
• አሁን ያለው ትውልድ አንድ መሪ ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ እንዲቀጥል አይፈልግም::
• ከ25 ዓመታት በላይ የኖሩ መንግሥታት እየተዋረዱ፤ እየተገፉ የወረዱበት እውነታ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው:: እኔ ህወሓት ምን እንደሚፈልግ አላውቅም::
• ህወሓቶች «አብይ አምባገነን ነው፤ ›ተጋሩ› እየተገደለ ነው» የሚሉት ነገር ሁሉ ውሸት ነው:: አንድ ነገር ልንገርሽ ፤ ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ እየተገደሉ፤ እየታፈኑ ያሉት የትግራይ ተወላጆች አይደሉም፤ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው::
• በየዩኒቨርሲቲውና በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ተፅዕኖ ሲደርስባቸው ያየነው አማራና የኦሮሞ ተማሪዎችን ነው::
• ህወሓት ምን እንደሚፈልግ ግልፅ አይደለም:: እዚህ አካባቢ በሰላም እንዲቀጥል የተፈቀደለት ብቸኛው መንግስት ህወሃት ብቻ ነው፤ ግን እየበጠበጠ ያለው ራሱ ነው::
• እውነቱን ለመናገር የባድመ ጦርነት የመሬት ጥያቄ አልነበረም:: ኢሳያስን የማደከምና ኤርትራን የመምታት ፍላጎት ስለነበር ነው::
• የኢትዮጵያን ህዝብ በኤርትራ ላይ ማስነሳት የምትችይው «መሬትህ ተወረረ» ስትዪው ብቻ ነው:: በወቅቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በሻቢያ ላይ ትንሽ ቅሬታ ነበረበት::
• አገሪቱን ይመራው የነበረው ህውሃት በወቅቱ ኤርትራ ላይ የተጠቀመው የጦርነት ፖሊሲ ነው:: በወቅቱ የመሪና የአመራር ችግር ነበር::
• ላለፉት 20 ዓመታት ጦርነትም ሆነ ሰላም ሳይኖር የተቆየበት ዓመታት በተለይ የትግራይን ህዝብ የጎዳበት ሁኔታ እንደነበር እሙን ነው::
• ይህንን ሁኔታ ማስቀረት የቻለው የአብይ አስተዳደር ነው፤ ህውሃት20 ዓመት ሙሉ ችግሩን ታቅፎት ከመኖር ውጭ መፍትሄ ማምጣት አልቻለም:: ስለዚህ በዶክተር አብይ ትልቅ ለውጥ መጥቷል ብሎ በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል::
• የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሓት የሚፈልገው ሰላም ብቻ ነው:: የተጣለ አስተሳሰብ( አይዶሎጂ) ይዘህ፤ የ60ዎቹ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የቀረፀልንን አጀንዳ በ2012 ላለው ትልውድ ልታቀርበው አትችልም:: ዘመኑን የሚመጥን ሃሳብ ይዘህ መምጣት ይገባሃል የሚል መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ::
• በሌላ በኩል አንቀፅ 39 ላለፉት 27 ዓመታት ተነስቶ አያውቅም፤ አሁን ለምንድንው በትግራይ አካባቢ የሚነሳው? ህወሓት ከስልጣኑ ስለተባረረ ነው?
• በእኔ አስታሳሰብ ትግራይ ብትገነጠል መጀመሪያ የምትጎዳው ኢትዮጵያ ናት የምትመስለኝ:: ምክንያቱም ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ትግራይ ውስጥ አለ:: እሱን እናጣለን:: ምክንያቱም ቁጥራችን የሚጀመርው ከህዝብ ነው:: ስለመሬት፣ ስለማዕድንና ስለሃብት ከማውራታችን በፊት ልናጣ የምንችለውን ህዝብ ነው ማሰብ የሚገባን::
• በሁለተኛ ደረጃ በምትቀጥለዋ ትግራይ ምን ሊፈጠር ይችላል? ብዬ ሳስብ ደግሞ እሰጋለሁ:: ምክንያቱም በአንድ በኩል በጣም የመረረ ጥያቄ የሚያነሱ የአማራ ክልል ሰዎች አሉ:: ጅምላ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተፈፅሞብናል የሚሉ አሉ:: በኤርትራ በኩል ያለውም ስሜት ጥሩ አይደለም::
• በታሪክ በተደጋጋሚ ከህወሓት ዘላቂ ግንኙነት ሊኖር እንደማይችል ኤርትራውያን ጠንቅቀው ያውቃሉ:: በምትገነጠል ትግራይ ውስጥ ኤርትራውያን በጣም ነቅተው የሚጠብቋት አገር ነው የምትሆነው::
ምንጭ አዲስ ዘመን ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም