በ2 አመት አብይን አምባገነን ያሉት ሕወሓቶች እነሱ 27 አመት ምን እንደነበሩ ሊነግሩን ይገባል።

ሕወሓት አሁንም ቅርሻቷን መትፋቷን ቀጥላለች። በፖለቲካ ኩርፊያ ስልጣን አይገኝም፤ ሐገርም አይሸበርም።
ስልጣን ካላገኘን ካልዘረፍን ካልገደልን እንቅልፍ አይወስደንም የሚሉ የሕወሓት ሹመኞች በፈበረኳቸው ሚዲያዎች በኩል የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች ምን ያህል ለሕዝብ ያላቸውን ንቀትና ለሃገር ያላቸውን ጥላቻ እያስመሰከሩበት ነው። በ2 አመት አብይን አምባገነን ያሉት ሕወሓቶች እነሱ 27 አመት ምን እንደነበሩ ሊነግሩን ይገባል።
እፍረት፣ይሉኝታና ይቅርታን የማያውቁ ደናቁርቶቹ ሕወሓቶች ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የገቡበትን ኩርፊያ ይዘው ጥላቻቸውንና ክፋታቸውን እየተፉ ነው። ሕወሃቶች ብልጽግናን እንደሐገር ወይም ሕዝብ ወስደው ሳይሆን ስልጣኑን ለምን ተነጠኩኝ በሚል እደምታ አደገኛ ተግባራትና እኩይ ፕሮፓጋንዳ ላይ ተሰማርተዋል።
ሕወሓት የፖለቲካ ኩርፊያቸውን ለሐገር ክሕደት አውለውታል። በዓባይ ጉዳይ ላይ ከግብፅ ጎን እስከመቆም ደርሰዋል። ትግራይንም ለመገንጠል ከራሳቸው ጭምር አጋር ፓርቲዎችንም ፈልፍለው ስለ ሐገር መገንጠል የድሮ ቅርሻታቸውን መትፋት ጀምረዋል። ሐገር የማስገንጠልና የመገንጠል የጥላቻ ስራቸውን ከድሮ ጀምረን የምናውቅ ቢሆንም ይህንኑ ጥቅማቸው ሲቀር ማውራት ጀምረዋል።
ይህ ሁሉ ችግራቸው ስለ ትግራይ ሕዝብ አስበው ሳይሆን ስልጣን በማጣታቸው፣ ዝርፊያው ስለቀረባቸው ፣ መግደልና ማሰር ሱስ ስለሆነባቸው፣ ወዘተ ነው። ሕወሓቶች ቆም ብለው ማሰብ ካልጀመሩ በለውጡ ወቅት በአንገታቸው የገባላቸውን ሸምቀቆ እያጠበቁ እንደሚገኙ ሊያውቁት ይገባል። #MinilikSalsawi