የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ፌደራልና ትግራይ ክልልን ለመሸምገል ወደ መቀሌ ሊጓዙ ነው።

52 አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ልዑክ ወደ መቀሌ የሚያደርገው ጉዞ ምክንያት በአገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ለማርገብ ያለመ መሆኑ በቡድኑ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ አባ ማቲያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪስ እና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ የሰባት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደሚሳተፉ ሰምተናል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ከዚህ ቀደምም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሰላም ጉዞ እንቅስቃሴ ያደርጉ እንደነበር ያመለከቱት የጉባኤው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀጂ መስዑድ አደም አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ የሃይማኖት አባቶችንና የሀገር ሽማግሌዎችን ጣልቃ ገብነት የሚፈልግ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሃይማኖት መሪዎቹ በተጨማሪ፣ የሀገር ባለውለታ የሆኑ ታዋቂ ሰዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በቡድኑ ውስጥ እንደሚሳተፉ የዚህ ጉዞ ሐሳብ ጠንሳሽና አስተባባሪ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ነው ፡፡የቡድኑን የጉዞ ወጪ በተመለከተ፣ ሙሉ ወጪው ጉዳዩ ያገባናል ባሉ ባለሀብቶች እንደተሸፈነ፣ ከዚያም ውስጥ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሤ የቡድኑን የመጓጓዣ ወጪ እንደሸፈነ  በነገው ዕለት የሀገር ሽማግሌዎች የሚሄዱበት የትግራይ ክልል እንግዶች እንደሚመጡበት እንደተነገረው ተሰምቷል፡፡ቡድኑ ነገውኑ ጉዳዩን ጨርሶ ይመለሳል ተብሏል፡፡የሃይማኖት አባቶቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ ለተመሳሳይ ተልዕኮ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የመጓዝ ዕቅድ እንዳለውም ተሰምቷል፡፡
“አንዳንድ ወገኖች ሽማግሌም ሆነ ትልቅ ሰው የለም ወይ?” እንደሚሉ የጠቀሱት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል የሚታየውን አተካሮ አለዝቦ የማስታረቁ ሃሳብ ሁለቱም ተቋማት በየበኩላቸው ተነጋግረው ከሁለቱም ወገን የመነጨ መሆኑም አመልክተዋል።
ዋና ዓላማቸው ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገር መሆኑን በማመልከትም ለዚህም ይሁንታቸውን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።የብልፅግና ፓርቲ የሕዝበ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ ስለዚህ ጉዳይ ፓርቲያችን የሚያውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡