ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የፈረጀው አዋጅ ተነሳ።

ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የፈረጀው አዋጅ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው አፀደቀው ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለፓርላማው ልኮ ያፀደቀው  የአዋጅ ማሻሻያ የድርጅቶቹ አባላት በኢትዮጵያ ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት ተሳትፏቸውን እንዲያጎለብቱ ለማድረግ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ሶስቱን ድርጅቶች ማለትም የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባርና ግንቦት 7ን በሽብርተኝነት የሚፈርጅ አዋጅ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡