በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 – ከበሽታው ያገገሙ 231 – ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 14 ደርሷል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመርያው የ30 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን ሁለተኛዋ የ56 ዓመት በአዲስ አበባ የተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አራት ሰዎች (ስድስት ከኦሮሚያ ክልል እና ስምንት ከሶማሊ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 231 ነው።