በቅዳሜው የቦምብ ጥቃት ቴሌና መብራት ሐይል እጃቸው እንዳለበት መረጃ መገኘቱ ተሰማ

ዶ/ር አብይንና ህዝቡን ለማጥቃት በተሞከረው የቅዳሜው የቦንብ ጥቃት ላይ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መብራት ሃይልና ቴሌ እጃቸው እንደነበረበት ተሰምቷል።

ይህ ኦፕሬሽን በጣም በረቀቀ ሁኔታ ታስቦበት ሊፈፀም የነበረ ሚሽን መሆኑን እንረዳለን ። ሆኖም ከአእምሮ በላይ በሆነ ሁኔታ የረቀቀው ሚሽን ከሸፈ ። ግን ቴሌና መብራት ሃይል በዚህ ውስጥ እንደነበሩበት መስማት ያማል ።

ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ቦምብ ከመወርወር ጀምሮ ሂደቱ እንዲስተጓጎል በወቅቱ መብራት እንዲጠፋ እና የቴሌኮም ኔትወርክ የማቋረጥ ተግባር መፈፀሙ ተረጋግጧል ።
የኢኮኖሚ አሻጥር በተደራጀ አኳኋን በመስራት የኑሮ ውድነት እንዲባባስና የተለያዩ ህዝባዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የተቋቋሙ ተቋማት አስፈላጊውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እየተደረገ ነው ። ስለሆነም ይህን መስሉን ሳቦታጅ ለማክሸፍና ፈፃሚዎቹንም ለህግ ለማቅረብ አዲስ ኮሚቴ ተቋቁሟል ። ምንሊክሳልሳዊ