አሶሳ የክልሉ ፖሊስ ትጥቅ የፈታ ሲሆን የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የቤንሻንጉል ክልል የፖሊስ አዛዥ አብደላ ሸኸዲን እና የልዩ ሀይል አዛዥ ረጅብ በመከላከያ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በርካታ መሳሪያም ከቤታቸዉ ተይዟል።

አሶሳ ዛሬ ከሰሞኑ በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ። ትናንትና ከትናንት ወዲያ እንደነበረው የጥይት ድምጽ መሰማት አቁሟል ። መከላከያ ከገባ በኋላ ከፀጥታ አንፃር ዛሬ የተሻለ ቢሆንም ሱቆች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው ፡ፀጥታውን ለማስቆም ቸልተኛነት አሳይቷል በሚል ስሙ እየተነሳ የሚገኘውን የክልሉ ፖሊስ ትጥቅ እንዲፈታ ተደርጓል ።አሶሳ ዛሬ አንፃራዊ ሰላም አለ!

ከተማዋ ዛሬ ሰላም ሆናለች። በከተማዋ ምንም አይነት የረብሻ እንቅሥቃሴ የለም የፖሊሥ እነ የመከላከያ መኪና ብቻ ሲዘዋወር ይታያል። ብዙ ሰው ወደ ሆሥፒታል እየተጓዘ ነው። ሆኖም ወጣቶቹ በየቤቱ በር ላይ ቁመው በፖሊሥ ላይ ተቃውሞ ያሰማሉ፡፡ፖሊሥ ሌባ ፖሊሱን አውርደው እያሉ በመከላከያዎች ላይ የቅሬታ ድምፅ ያሰማሉ፡፡

አስከሬን የጫነ ግን መኪና ከሆሥፒታል ይወጣል (አሥከሬን ጭኖ ወደ ኦሮምያ እየሄደ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል) ሰው ከኦሮምያ ይመጣልእና ረብሻው ይነሳል የሚል ሥጋትም አለ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭቱን ያነሳሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

በክልሉ በገንዘብ ተደልለው ግጭት ያነሳሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራና የማጣራት ስራ እየተደረገባቸው ነው፡፡

እስከ አሁን በግጭቱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር 9 ደርሷል፡፡