በአሶሳ ውጥረቱ ተባብሶ ሕዝብ ጭንቅ ውስጥ ነው።

ከትናት በስቲያ ምሽት ጀምሮ በአሶሳ ከተማ የተቀሰቀሰው ሁከትና ረብሻን ለማባባስ በሚመስል መልኩ በአንድ አይሱዙ መኪና ተጭነው ወደ አሶሳ ከተማ ሊገቡ የነበሩ ሽፍቶች ማምሻውን በመከላከያ ሃይል በቁጥጥር ስር ዋሉ ..
እነዚህ ወደ ከተማዋ ሊገቡ ሲሉ የተያዙት የበርታ ብሄረሰብ ሁከት ፈጣሪዎች በአሁኑ ሰአት በመከላከያ ሃይል ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያስረዳል. በአሶሳ የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ የክልሉ የጸጥታ ሃይል ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ግዴታውን በአግባቡ ሊወጣ ባለመቻሉ የመከላከያ ሃይል እስከሚገባበት እስከዛሬ ከሰአት ድረስ ቀላል የማይባሉ ዜጎች ለጉዳትና ለሞት ተዳርገዋል ።

በአሶሳ አንድ ሰው ሲሞት ፤ ሶስት ሰወች በጥይት ተመትተው ቆስለዋል ።

የምእራብ እዝ የላካቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቦታው የደረሱ ሲሆን በከተማው የሚገኙ የሕወሓት ባለሐብቶች ያስታጠቋቸው የበርታ ተወላጆች ሰራዊቱ ላይ ቶክስ ከፍተዋል።

ብጥብጡ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል። ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የታገዱ በርታዎች አልተለቀቁም በሚል በሌላው ማኅበረሰብ ላይ ጥቃት ተከፍቷል።

ሕዝቡም አጸፋ መስጠት በመጀመሩ መከላከያ ገብቶ የአዋሳው እልቂት ከመደገሙ በፊት ችግሩን ለመቆጣጠር እየሰራ ቢሆንም የጥይት ድምፆች ከተማዋን እያናወጧት ነው። Minilik Salsawi