የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባል

የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

ኢትዮጵያ የአልጄርስን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ካለቅድመ ሁኔታ ተቀብላ ለመተግበር መወሰኗን ተከትሎ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የልኡካን ቡዱን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ መናገራቸው ይታወሳል።