የአፋር ሕዝብ ለዶክተር አብይ ያለውን ድጋፍ በነቂስ አደባባይ ወጥቶ ገልጿል። በዚህ የተበሳጨው የክልሉ መሪ ፓርቲ አለቃውን ሕወሓትን ይዞ በሕዝቡ ላይ ማሴር መጀመሩ ታውቋል።
ለቅድመ ጥንቃቄ የህወሓት ቡዱኖች ሽንፈታቸውን ባለመቀበል በየቦታው እኩይ ተግባር ለመፈፀም ስሯሯጡ ይታያሉ፡፡
በተለይ በአፋር ክልል ዋና ዋና ከተሞች በየሳምንት ምስጢራዊ ስብሰባ በማድረግ በአፋር ክልል ላይ ተቃውሞ ሠልፍ ለማስኬድ ከፍተኛ ዝግጅት በማደረግ ላይ መሆናቸው ትክክለኛ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በተለይ በአይሳኢታ፡ በሎግያ፡ በዲቾኦቶ፡ ገዋኒ፡ ሚሌ፡ አዋሽ፡ዱብቲ፡ አብዓላ ወዘተ ከተሞች ላይ የሠልፍ ኘሮግራም ለማድረግና ከመንግስት ፍቃድ ለመውሠድ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
ይህ ማለት ህወሐት ለ27 አመታት በአፋር ህዝብና ንብረት ላይ ያደረሰው ብዝበዛና ጭቋና ከምንም ሳይቆጥረው ነገም ወደፊትም በአፋር ህዝብ ላይ የጭቋና ቀንበር ማስቀጠል መፈለጉን የሚያሳይ እብሪት መሆኑን ያሳያል፡፡
አብዴፓ ለአፋር ወጣቶች በየቦታው የሠልፍ ፍቃድ ጥያቄዎችን ውድቅ እያደረገ በልዩ ሐይልና በፖሊስ አካላት ለሰልፍ የሚወጣውን ወጣት እየደበደበ፡እያሰረ ባለበት ወቅት ለመንፈስ እባቱ ለህወሓት ካድሬዎች የሰልፍ ኘሮግራም ፍቃድ የሚሠጥ ከሆነ በክልሉ ለሚፈጠረው ችግር ከወዲህ የህወሓት መራሹ አብዴፓ መሆኑ ከወዲሁ መታወቅ መቻል አለበት፡፡
ሰለዚህ እንዲህ አይነት ችግር ሆን ተብሎ በህወሓት የተሴረ ሥራ በመሆኑ ህይወሐትና የትግራይ ህዝብ ለይቶ የማያት እይታችን መፍስቶ መገኘት መቻል አለበት፡፡ ለማንኛውም ነገሩ ከመከሠቱ በፊት የክልላችን ሠላም በኛው በራሳችን እጅ ነውና በጠንቀቅ እንጠብቅ፡፡ አብዴፓ ለህወሓት እኩይ ተግባር ለሚደረገው ሠልፍ እውቅና መሰጠት የለበትም ባይ ነኝ፡፡