ቦምብ በሻንጣ የጫነችው የፖሊስ መኪና (ፖሊስ ኢት 0384 ET) ሆን ተብሎ እንድትቃጠል ተደርጋለች።

መኪናዋ…
ይህች ላንድክሩዘር መኪና (ፖሊስ ኢት 0384 ET) ከመቃጠሏ በፊት የፖሊስ ደንብ ለብስ የለበሱ ሰዎችን ጭና መስቀል አደባባይ ነበረች።


ኋላ ላይ…ቦንብ ከፈነዳ በኋላ በውስጧ ቦንብ የያዘ ሻንጣ መገኘቱን ሰምቻለሁ።
መኪናዋ ከመቃጠሏ በፊት መለያ ታርጋዋን ወጣቶች ገንጥለው ይዘውታል።

ታርጋውን ከነገጠሉት ልጆች መካከል አንደኛው ልጅ ላንድክሩዘሯ የፖሊስ መኪና ውስጥ ቦንቦችና ሌሎችም ተቀጣጣይ ነግሮች እንደነበሩ ገልጾልኛል።
መኪናዋን ማን እንዳቃጠላት አላወኩም። ባትቃጠል ኖሮ ተጨማሪ ማስረጃዎች በውስጧ ሊገኙ ይችል ነበር።

የዛሬውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓል።