የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሊሰበሰብ ነው
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሚያዝያ 02 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
በልዩ ስብሰባውም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብም መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል።
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው እነዚህና ሌሎችም አለም አቀፍ ስምምነቶች ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
(ኢ ፕ ድ)