መደበኛ ሰራተኞቼን አላሰናበትኩም ይህንን የማድረግ እቅድም የለኝም — የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Sheger FM : የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ ሰራተኞቼን አላሰናበትኩም የማሰናበትም ሀሳብ የለኝም አለ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ ድረገፅ እና በመደበኛ መገናኛ ብዙሃን ባልተገባ መንገድ ስለአየር መንዱ የሚወጡትን መረጃዎች በፅኑ ተቃውሟል፡፡
አየር መንገዱ ስሙን የሚያጎድፉ የበሬ ወለደ ወሬዎችን ያልተገቡ ሲል አውግዟል፡፡
መረጃዎቹም ሀሰት ናቸው ማለቱን ከአየር መንገዱ ሰምተናል፡፡
አየር መንገዱ መደበኛ ሰራተኞቼን አላሰናበትኩም ይህንን የማድረግ እቅድም የለኝም ብሏል፡፡
በኮቪድ 19 ሰበብ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ታይቶ በማይታወቅ መጠን ተጎድቷል ያለው አየር መንገዱ የኢትዮጵያ አየር መንድም የዚህ ቀውስ ሰለባ ከመሆን አላመለጠም ብሏል፡፡
በዚሁ ምክንያትም 87 ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቋረጡ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቫይረሱ ምክንያት ቋሚ ገቢውን ቢያጣም መደበኛ ሰራተኞቹን ግን የማሰናበት እቅድ የለኝም ብሏል፡፡
አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራዎች ባያቋርጥም 50 በመቶ ገቢው መቀነሱንም ተናግሯል፡፡
Source – sheger werewoch