የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኮርባንኪንግ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዝግ እንደሚሆን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ3 ቀናት ዝግ እንደሚሆን አስታወቀ
————————————————
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች ለኮርባንኪንግ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ስራ ለ3 ቀናት ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡
ከመጪው ሐሙስ ሚያዚያ 01 እስከ ቅዳሜ ሚያዚያ 03፣ 2012 ዓ.ም ድረስ የባንኩ ቅርንጫፎች የሚዘጉ ሲሆን በእነዚህ ቀናት የኤቲኤም ማሽኖች፣ ፖስና ሲቢኢ ብር የተለመደ አገልግሎት እንደሚሰጡ ባንኩ በይፋዊ ማህበራዊ የትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡
የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ደንበኞች የቆጠቡትን ገንዘብ በቦታ ሳይገደቡ ከየትኛውም ቅርንጫፍ ገቢና ወጪ እንዲያደርጉ እንዲሁም የተለያዩ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃም በነጻ የደንበኞች የግንኙነት ማዕከል 951 መደወል እንደሚቻልም ባንኩ አስታውቋል፡፡
Walta