የመንግስት ውሳኔዎችን በማያከብሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

በመንግስት የተላለፉ ውሳኔዎችን በማያከብሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል- ኢ/ር ታከለ
(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር በወሰነው መሰረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ስራው መጠናቀቁን ኢጅነር ታከለ ኡማ ገለፁ።
ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ነጋዴዎችና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎችም መንግስት የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የወሰነውን ውሳኔ ማክበር ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የተወሰኑ ውሳኔዎችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ይመራሉ፤ እርምጃዎችንም መወሰድ ጀምረናል ብለዋል ኢንጅነር ታከለ ኡማ።
የአትክልት ተራ ከነገ ጀምሮ እንደሚዘጋ የገለፁት ምክትል ከንቲባው በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ሥራ ይጀመራል ነው ያሉት።
በመሆኑም ነጋዴዎች በህግና መመሪያ እንዲመሩ ያሳሰቡ ሲሆን ነዋሪዎችም ህግን የማስከበር ስራው ተባባሪ ሆነው ጃንሜዳ በመሄድ እንዲገበያዩ አሳስበዋል።