በአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ቤንዚን ለማግኘት ለቀናት የተራዘመ ሰልፍ ለማድረግ ተዳርገዋል።

የተዘጋው የሱዳን ድንበር በኢትዮጵያ የቤንዚን እጥረት አስከትሏል

DW : የኮሮና ተኅዋሲ በፈጠረው ስጋት የተዘጋው የሱዳን ድንበር በኢትዮጵያ የቤንዚን ፍጆታ አቅርቦት ላይ እጥረት አስከትሏል።ይህን ተከትሎም በአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ቤንዚን ለማግኘት ለቀናት የተራዘመ ሰልፍ ለማድረግ ተዳርገዋል።ኢትዮጵያ ሰማንያ በመቶ ያህሉን የቤንዚን ፍጆታዋን በጅቡቲ የምታስገባ ሲሆን ቀሪው ሃያ በመቶውን ግን በሱዳን በኩል ታስገባለች።በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የተፈጠረውን እጥረት ለመፍታት ከሱዳን ጋር በተደረገ ዲፕሎማሲያዊ ምክክር መፍትሄ ተገኝቶ ተሽከርካሪዎች ምርቱን ለማስገባት ተጓጉዘዋል ብሏል።