በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ ተጨማሪ ሰው አገገመ

በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ ተጨማሪ ሰው አገገመ:: ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 65 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ተካሂዶ ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል።

 

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 65 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ተካሂዶ ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ ሆነዋል።
በለይቶ መስጫ ማዕከል ውስጥ 25 የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መኖራቸውን እና ከዚህ ቀደም ከሕመሙ ማገገማቸው ከተገለጸው ሁለት ሕሙማን በተጨማሪ ሌላ ሦስተኛ ሰው ማገገሙን ተናግረው አንድ ታማሚ በጽኑ ሕሙማን ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል።