አዲስ አበባ ታክሲዎች የነዋሪዎችን ጤንነት ለመጠበቅ ቸልተኝነት ስላሳዩ ከስራ ይታገዳሉ ተባለ

በአዲስ አበባ ታክሲና ባጃጆችን ስራ ሊያስቆም እንደሚችል የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስጠነቀቀ፡፡

ሸገር 102.1

 

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተሽከርከሪዎች ትርፍ ከመጫን እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ አውቶሰብሶችም በወንበር ልክ ብቻ እንዲጭኑ መደረጉ ይታወቃል፡፡

 

ይሁንና የከተማ አስተዳደሩ አደረግሁት ባለው ቁጥጥር ታክሲዎችና ባጃጆች ትርፍ እየጫኑ መሆኑን ታዝቤያለሁ ብሏል ስለሆነም በፍጥነት የማያስተካክሉ ከሆነ የነዋሪውን ጤንነት ለመጠበቅ ከስራ ውጭ ለማድረግ እንደሚገደድ የከንቲባ ፅ/ቤት አስጠንቋል