በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩት 16 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሙሉበሙሉ አገገመ

ENA : በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩት 16 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሙሉበሙሉ አገገመ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ከነበሩት 16 ሰዎች መካከል አንዱ ሙሉበሙሉ ማገገሙን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማቆያ የሚገኙ 13 ታማሚዎች መቅረታቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩት 16 ሰዎች መካከል ሁለቱ ጃፓናውያን ወደ ሀገራቸው ሄደዋል ብለዋል፡፡እስካሁን 797 ሰዎች ላይ የላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል፡፡