ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች ለማምለጥ ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ

ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች ለማምለጥ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ገለጸ።
 
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እንዳስታወቀው፤ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉ የህግ ታራሚዎች ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል።
 
በዚህም ማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ አንድ ዞን እሳት ተነስቶ የነበረ ሲሆን በማረሚያ ፖሊስ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሏል።
 
የማምለጥ ሙከራ ያደረጉት የህግ ታራሚዎች በህግ የሚጠየቁ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ምንጭ ኢዜአ
……………………..
አንድ ጉዳዩን ሚያውቅ ግለሰብ መረጃ እንደሚያመለክተው ታራሚዎቹ “በቅርቡ በርካታ ሰዎች ከእስር ተፈተዋል፣ በሽታ እንዳያጠቃን እኛንም ፍቱን፣ እየመረጡ መፍታት አግባብ አይደለም” ብለው አድማ አርገው እንደነበር እና በዚህም ከፍተኛ ግርግር ነበር