" /> ከውጪ ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ አቅም የሌላቸው መንገደኞች በ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲያርፉ ተደረገ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ከውጪ ወደ ሐገር ውስጥ የሚገቡ አቅም የሌላቸው መንገደኞች በ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲያርፉ ተደረገ።

ሸገር 102.1 ራዲዮ
መንግስት ባዘዘው መሰረት፣ አቅም የሌላቸው መንገደኞች ለ14 ቀናት በቦሌ መሰናዶ ተማሪ ቤት እንዲያርፉ ተደርጓል፡፡
በመንገደኞቹ ዘንድ የተፈጠረውን ግርግር ሸገር 102.1 ራዲዮ ተመልክቷል።ይህንኑ ጉዳይም ይዘን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያን ለማግኝት ሞክረናል።ሸገር ለግዜው መምሪያውን ባያገኝም ይህንኑ ስራ ያመቻቸውን የከተማ መስተዳድሩን ስለተፈጠረው ችግር ጠይቋል።
የከተማ መስተዳድሩ ፕሬስ ሴክሬተርያት ፌቨን ተሾመ መልሳቸውን ለሸገር አስረድተዋል።እርሳቸውም እንዲህ ያለው ነገር ዳግም እንዳይፈጠር ከነገ ጀምሮ የሚገቡ መንገደኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በቂሊንጦ ከፍተኛ ተማሪ ቤት ያርፉሉ ብለዋል።እነዚህም ዩኒቨርስቲዎች የተሻሉ እንደሆኑ እና የራሳቸው ምቹ አገልግሎት መስጫ አላቸው ሲሉ ለሸገር ነግረዋል።
ከተማ መስተዳደሩ ከውጭ ወደ ሐገር ቤት ለሚገቡ መንገደኞች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና ከቂሊንጦ ተቋም ሌላም ተጨማሪ ቦታ ተሰናድቶላቸዋል ብሏል።ቢሮው ዛሬ በአንዳንድ ማረፍያ ቦታዎች የተፈጠሩት ችግሮች እንዳይደገምም ከነገ ጀምሮ የበረታ እንሰራለን ብሏል።

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV