ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን በይፋ ተናግረዋል (ቪድዮ )

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮዽያ ጋር የሚደራደር የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልክ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ ጋር “ገንቢ ውይይት” ለመጀመር ወደ አዲስ አበባ ልዑካን እንደሚልኩ ዛሬ ጠዋት በኤርትራ ቴሌቪዥን ቀርበው እንዳሳወቁ በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር በየነ ርዕሶም ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂም በትዊተር ገፃቸው ይህንኑ አረጋግጠዋል።