ሕዝቤ ሆይ መልካም መሪ ሰጥቶሃልና እድሉን ተጠቀምበት – መምህር ልኡልቃል አለሙ

የተከበሩ መምህር ልኡልቃል አለሙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ሰዎችና ለሃይማኖት አባቶች ፣ በዚህ ወቅት ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የጀመሩትን የሰላም፣ የፍቅር፣ የኢትዮጵያዊነትና የአንድነት እንቅስቃሴ እንዲደግፉ አክብሮታዊ መልእታቸውን አስተላልፈዋል። የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ እግዚአብሄር ነውና፣ በዶ/ር አብይ በኩል መልካም ነገር ለኢትዮያ እንዲመጣ ያደረገው ፈጣሪ መሆኑን ገልጸው፣ ከዶ/ር አብይ ጋር መቆም ከፍቅርና አንድነት ጎ መቆም እንደሆነ ነው ያሰመሩበት።

መምህር ሉልቃል ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው አቅርበናል

———————————

ከጠቅላይ ምንስቴር ዶ/ር ዐቢይ ጋር በመቆም በጋራ ለአገራችንን አብረን እንሥራ!«ዓመፃን የሚያደርጉ ሁሉ ከዚያ ወደቁ፤ወድቀዋል መቆምም አይችሉም።» መዝ 35፥12ከሁሉ አስቀድሞ በወላይታና በወልቂጤ ስለጠፋው ሕይወትና ንብረት የተሰማኝን አዘን እየገለጥኩ መልክቴን ለወገኖቼ እንደሚከተለው አስተላልፋለሁ።

ሀ) ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፦

ሕዝቤ ሆይ!በዚህ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር Oቢይ ጋር መቆም ለኢትዮጵያ ሰላም፣ነጻነት፣አንድነትና እኩልነት መቆም መሆኑን ልታውቅ ይገባል።ምክንቱም፦

1ኛ ሕማምህ ከሚያመው ውርደትህ ከሚሰማው፣ እግዚአብሔር ከሰጠህ መሪ ጋር መቆም በዚህ ጊዜ እጅግ አስፈላጊ ነው፤ በሀገራችን በኢትዮጵያም ሆነ ለጉብኝት ሄደበት አገር ሁሉ «ሕዝቤን ልቀቅ» እያለ ከሥር የሚያስፈታ መሪ ለኢትዮጵያ ያስፈልግ ነበርና ፣ የሕዝቡን ሰቆቃና ውርደት የተመለከተ ፈጣሪ፣ ዶ/ር ዐቢይን መሪ አድርጎ አሥነቶልሃልና፣ ከመሪህ ጋር የአገርህን ሰላምና አንድነት በመጠበቅ መሪህን አግዘ፤

2ኛ ሕዝቤ ሆይ! ለሀገርህ አንድነት ሰላም የሚያስብ ፣ጠባብነትን የሚጠየፍ፣አንድነትን እኩልነትን የዜጎችን መብት መከበር አላማው ያደረገ መሪ እግዚአብሔር ሰጥቶሃልና እድሉን ተጠቀምበት፤ አብረኸው ቁም!

3ኛ ሕዝቡን ሕዝቤ የሚል በእኩልነትና በፍቅር ሕግ የሚያምን መሪ ሆኖ ከተነሣው መሪህ ጋር በመቆም በኢትዮጵያ ፍቅር እንጅ ጥላቻ እንዳይሰለጥን ፣የሰላም ሐዋርያ ከሆነው መሪህ ጋር ስለ ኢትዮጵያውን ፍቅርና አንድነት የምትችለውን ያክል ዋጋ ለመክፈል ተነሥ!

4ኛ ሕዝቤ ሆይ! የወደቅህበትና የደረሰብህን ፈተና የአየና የተረዳ መሪ አስነሥቶላሃላና እድሉ እንዳያመልጥህ በአንድነት በመቆም ከመሪህ ጋር አገርህን ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ ተነሥ!

ለ) ለተፎካካሪ የፖለቲካ መሪዎች

ከዶ/ር ዐብይ ጋር ለመሥራት ብቻ ሳይሆን ዶ/ር ዐቢይ የጀመረውን አገርን በአንድነትና በእኩልነት ለማዳን የሚሰራውን ሥራ ለማደናቀፍ የታገሉትን በመመከት የሥራ ዕድል እንዲኖረው አብራችሁት ልትቆሙ ይገባል፤

ምክንያቱም፦

1ኛ በዲሞክራሲና በእኩልነት የሚያምን መሆኑን በግልጽ ስለተናገረ፣በሥራም አቋሙን የገለጠ መሪ ስለሆነ፤

2ኛ በአገራችን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ በንቃተኅሊናንና በጎ ሰውነትን አስተባብሮ የያዘ ብልህ መሪ ስለሆነ፤

3ኛ የጥላቻና የበቀል ፖለቲካን የሚጸየፍ ስለሆነ፤

4ኛ በብሔራዊ እርቅና መግባባት የሚያምን መሪ ስለሆነ ልትደግፉት፣የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት እንቅፋቶችን በማንሳት ሥራው በቃልም በጽሁፍም በተግብርም ልታግዙት ይገባል፤

ሐ) የሃይማኖት መሪዎች

ከጠ/ም ዶ/ር Oቢይ ጋር በመቆም አገራችንን አብራችሁ እድትሰሩ ጥሪየን አቀርባለሁ፤ ለምን?

1ኛ  ለትውልድ በቃሉና በሕይወቱ መልካም ዓርዓያና ምሳሌ የሚሆን መሪ ስለሆነ፤

2ኛ  እግዚብሔርን የሚፈራ ሕዝቡን የሚያከብር መሪ ስለሆነ፤

3ኛ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩልነትና ነጻነት የሚተጋ መሪ ስለሆነ፤

4ኛ ስርቆትንና የፍትህ መዛባትን የሚጸየፍ መሪ ስለሆነ፤

5ኛ ሚሰማና የሚሰማ መሪ ስለሆነ፤

6ኛ የፖለቲካ መሪ ብቻ ሳይሆን በሞራልም ትልውልዱን የመምራት ብቃት ያለው መሪ ሁኖ ስለተነሳ

የሃይማኖት መሪዎች በጸሎት፣ ሕዝቡን ለሰላምና ለፍቅር በማስተባባር አብረነው እንድንሰለፍ ጥሪየን አስተላለፍለሁ፤

ከጠ/ም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር መቆም ከኢትዮጵያና ከትዮጵያውን አንድነትና ክብር ጋር መቆም ነው!

 

ከእውነት ጋር እንሰለፍ!

እግዚብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

አንብበው ሲጨርሱ ለሌላው መልክቱን ሼር ያድርጉ።

ሰላም ለክሙ