የኹለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ደም በግፍ የፈሰሰበት የ“24 ቀበሌ” ቅዱስ ቦታ ለቤተ ክርስቲያን ተሰጠ፤ ቅዱስ ፓትርያርኩ ነገ ከቀትር በኋላ ዕብነ መሠረት ያስቀምጣሉ

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ል ከንቲባ ታከለ ዑማ፣ ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያርኩ ተገኝተው፣ ባለፈው ታኅሣሥ 24 ለ25 አጥቢያ ጨለማን ተገን ባደረጉ የጸጥታ አስከባሪዎች፣ የኹለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ደም በግፍ የፈሰሰበት የ“24 ቀበሌ” ቅዱስ ቦታ፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሶ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራበት፣ አስተዳደሩ ያሳለፈውን ውሳኔ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስታውቀዋል፤ ውሳኔው የተላለፈው፣ የይዞታው ባለመብት ኾነው የቆዩት አቶ …