ሕወሓት በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ያበቃለት ቡድን መሆኑን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

 

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሕወሓት ከእንግዲህ የማያንሰራራ ያበቃለት ቡድን ነው ሲሉ ተናገሩ። የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት ከእንግዲህ በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ያበቃለት ቡድን መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ  በኤርትራ ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል።

“ አዲስአበባ ድረስ ታንክና መድፍ ይዘን የገባነው ለሁለቱ ህዝቦች ዘላቂ ጥቅም ስንል ነበር” ሲሉም ተደምጠዋል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት በኤርትራ ቴሌቪዥን በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በህወሃት አደፍራሽነት 25 አመታት የገጠማቸውን ኪሳራ የሚያስመልሱበት ግዜ ሩቅ እንዳልሆነም ነው የተናገሩት።