124ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተከበረ

 

124ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ እና በአድዋ ከተሞች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ ፡፡ለዓድዋ ድል ክብር ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 12 ሰአት ላይ ከእንጦጦ መድፍ በመተኮስ ነው በዓሉ መከበር የጀመረው፡፡ኢትዮጵያውያን በህብረት ወራሪውን የጣሊያንን ጦር ድል በነሱበት ዓድዋም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በዓሉ ተከበረ ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የዐድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በተመለከተ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልእክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዶክተር ዐቢይ በመልእክታቸው፥ ዐድዋ በየትውልዱ እየተመነዘረ ለብልፅግና ጉዟችን ልንጠቀምበት የምንችለው ትልቅ ሃብታቸን ነው ብለዋል።

Image may contain: 1 person, outdoorአድዋ ኢትዮጵያዊያን አንድም ብዙም መሆናችንን ያሳየንበት ታሪክ ነው፤ በባህል፣ በቋንቋ፣ በብሄር፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በእምነት የየራሳችን ማንነት አለን። ይህ ማንነታችን በሀገራችን ውስጥ ተገቢውን ቦታ እንዲያገኝ ታግለናል፣ እንታገላለን። ከዚህ በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊ ያሰኘን አንድነትም አለን ሲሉም ጠቅሰዋል።

በአዲስ አበባ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከየአቅጣጫው መፈክሮችን በማንገብ፣ ጋሻና ጦር በመያዝ እንዲሁም ነጋሪት እየጎሰሙ ወደ ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ አቅንተዋል።በማለዳው ከሜክሲኮ አደባባይና ለገሃር አቅጣጫ ወደ ሚኒልክ አደባባይ በሚወስዱ ሁሉም አቅጣጫዎች በርካታ ወጣቶች እና የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ ቦታው አቅንተዋል።

በጠዋቱ በሰዎች የተሞላው የዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ ወጣቶቹ የተለያዩ መፈክሮችን፣ ጋሻና ጦር አንግበው፣ ነጋሪት እየጎሰሙ የዳግማዊ ሚኒልክና የእቴጌ ጣይቱን ምስል የያዙ ቲሸረቶችን ለብሰው በፉከራና ሽለላ በአሉን እያከበሩ ነው።በጉዞው ወቅት በርካታ ወጣቶች፤ የአባትና እናት አርበኞችን ታሪክ ለማሰብ በሚል በባዶ እግራቸው ሲጓዙ ታዝበናል።የወቅቱን የአርበኞች ታሪካዊ ኩነት ለማስታወስም በአህዮች ስንቅ ጭነው ወደ ሚኒልክ አደባባይ በማምራት በዓሉን በልዩ ሁኔታ እያከበሩት ነው።በዓሉ እየተከበረ ባለበት ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ አርበኞች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Image may contain: one or more people, people standing, crowd, sky and outdoor

Image may contain: one or more people and outdoor

Image may contain: 3 people, people standing and outdoor

Image may contain: 1 person, standing, on stage and outdoor

Image may contain: 1 person, outdoor