ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ባአካባቢው ባለው ፀጥታ ችግር ምክንያት ለ15 ቀናት ትምህርት ለማቋረጥ መወሰኑን አስታወቀ፡፡

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ባአካባቢው ባለው ፀጥታ ችግር ምክንያት ለ15 ቀናት ትምህርት ለማቋረጥ መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ ለኢትዬ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ቴፒ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር ረጅም ጊዜ የቆዬ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራ ላይ ችግር ሳይፈጥር መቆየቱን ነግረውናል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተከሰተ ግጭት ባይኖርም በከተማው የሚሰማው ተከታታይነት ያለው የተኩስ ድምጽና የጸጥታ ችግር ተማሪዎችን ተረጋግተው እንዲማሩ ካለማድረጉ በተጨማሪ ፤ መምህራንም ከቤታቸው ወጥተው ወደ ዩኒቨርሲቲው መጥተው ለማስተማር እንዳይችሉ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የሴሚስተሩ ማጠቃለያ ፈተና ከመሰጠቱ በፊት ተማሪዎች ለ15 ቀናት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው እረፍት እንዲያደርጉ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት መወሰኑን ነው ፕሬዘዳንቱ የነገሩን፡፡

የጸጥታ ሁኔታው እንዲስተካከልም ለመንግስት አካላት ማሳወቃቸውንም ነግረውናል፡፡

ትምህርት የሚቋረጥበት ጊዜ ከተጠቀሰው ቀን በላይ ሊራዘም የሚችልበት አጋጣሚ አለ ወይ ብለን የጠየቅናቸው ፕሬዘዳንቱ፤ የአካባቢው የሰላም ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንና መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ኢትዬ ኤፍ ኤም