የክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ በፌደራል ስር እንዲጠቃለሉ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።
ውይይቱን ጽናት ኢትዮጵያ የተሰኘው የበጎ አድራጎት ማህበር ያዘጋጀው ሲሆን የክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎች ለአገራችን ሰላም ያላቸው ሚና በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይግኛል።
በኢትዮጵያ የዜጎች መፈናቀል፣የማምለኪያ ቦታዎች መቃጠል እና ሌሎች እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች እንዲቆሙ እና የህግ የበከላይነት እንዲረጋገጥ መፍትሔዎቹ ምን ምን ናቸው በሚል ላይ እንደሚያተኩር የውይይቱ አዘጋጆች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የህግ ምሁራን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎች፣ የጸጥታ እና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።
የክልል ልዩ ሃይሎች እና ሚሊሻዎች አሁን ካሉበት ፉክክር ወጥተው እንዴት ለአገር ግንባታ እናውለው በሚልም የመፍትሔ ሃሳቦች እንደሚነሱበትም ይጠበቃል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8