" /> የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የግንባታ ቦታ ተፈቀደላት | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የግንባታ ቦታ ተፈቀደላት

ቤተክርስትያኗ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የግንባታ ቦታ ተፈቀደላት – (ኢ.ፕ.ድ)

Image may contain: 1 person, standingየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለቤተክርስትያን መስሪያ የሚውል የግንባታ ቦታ ጥያቄዋ መልስ ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ዛሬ ምሽት በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ጋር በአቡዳቢ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፃ ቤተክርስትያኗ ለብዙ አመታት ስታቀርበው የነበረው ይህ ጥያቄ አሁን ላይ ምላሽ አግኝቷል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስት እና በሀገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰሩት ሰፊ ስራ ውጤቱ መምጣቱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱን አካላት አመስግነዋል፤ በሌሎች እምነቶች የሚነሱ መሠል ጥያቄዎችም በጊዜያቸው መልስ እንደሚያገኙ ጨምረው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይህንን ጥያቄ ለሶስት አስርት አመታት ያህል ስታቀርብ መቆየቷን መረጃዎች ያመለክታሉ።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV