በሐዋሳ ከተማ በሲዳማና ወላይታ ብሔር ተወላጆች መካከል የከረረ ግጭት ተፈጥሯል፡፡

በሐዋሳ ከተማ በዋናነት በሲዳማና ወላይታ ብሔር ተወላጆች መካከል የከረረ ግጭት ተፈጥሯል፡፡ የንግድ ቤቶች በግድ እንዲዘጉ እየተደረጉ ሲሆን በወላይታና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ድብደባና ወከባ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡

በቦታው ወደሚገኝ ግለሰብ ጋር ስልክ ደውዬ እንዳረጋገጥኩት በተለይ አሮጌ ገበያ በሚባለው አከባቢ ነዋሪዎች መስራትም ሆነ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በመሆኑም ነገሮች ከቁጥጥር ከመውጣታቸው በፊት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአስቸኳይ ምላሽ ሊሰጡ ይገባል፡፡

በተያያዘ ዜና በወልቅጤ ከተማ በሚኖሩ የጉራጌ ብሔር ተወላጆችና በከተማዋ ዙሪያ ባሉት የቀቤና ማህብረሰብ ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአሁን ሰዓት ከወልቂጤ ወደ ወሊሶ የሚደረገው የህዝብ ትራንስፖርት ተቋርጧል፡፡