“ከወንድሞቼ ከኤርትራ እና ሶማሊያ መሪዎች ጋር እገናኛለሁ፤ ከፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከፕሬዚደንት ሞሀመድ አብዱላሂ ጋር በመሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይኖረኛል፤ እንደሁሌውም ውዷ ከተማ አስመራ ቆይታችንን የሚያምር ታደርግልናለች” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ማምሻውን በኤርትራዋ ዋና ከተማ አሥመራ የተገኙ ሲሆን፣ በፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ በቆይታቸው ከፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ እና ከሶማሊያው ፕሬዚደንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር የሦስትዮሽ ውይይት የሚያካሂዱ ይሆናል።
ዶ/ር ዐቢይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ የተካተቱበት ከፍተኛ ልዑክ በመምራት አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
ዶ/ር ዐቢይ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ እና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር የሦስትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Source : Prime minister Office page