ህወሓት ምርጫውን ለማካሄድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአዎንታዊነት እንደሚመለከተው ገለጸ

DW : ይፋ በተደረገው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ማስፈፀሚያ ጊዜያዊ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡ ሀገራዊው ምርጫ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ የቆየው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ( ህወሓት) ምርጫውን ለማካሄድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአዎንታዊነት እንደሚመለከተው ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ምርጫውን በክረምት ወቅት ለማድረግ መርሐግብር መውጣቱ የአብዛኛውን ህዝብ ሁኔታ ያላገናዘበ ብሎታል፡፡ ለረጅም ዓመታት በትግራይ ክልል በተቃዋሚነት እየተንቀሳቀሰ የዘለቀው ዓረና ትግራይ በበኩሉ ከምርጫ ማስፈፀሚያ ጊዜያዊ መርሐግብሩ ይልቅ በክልሉ ያለው የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ እንደሚያሳስበው በሊቀ መንበሩ በኩል ገልጿል፡፡