ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፀድቃል ያሉት የኤክሳይዝ ቀረጥ ረቂቅ አዋጅ እያከራከረ እያወዛገበም ነው

DW : መንግስት ከውጪ በሚገቡ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ሊጥለው ያሰበው የኤክሳይስ ታክስ በህዝብ ማጓጓዝ እና የጭነት አገልግሎት ላይ ችግር ያስከትላል ባማለት ኢትዮ የተሽከርካሪዎች አስመጪ ባለቤቶች ማህበር አሳሰበ።ረቂቅ ህጉ የቤት አውቶሞቢሎችን ብቻ ሳይሆን የህዝብ ማመላለሻ እና የጭነት ተሽከርካሪዎችንም የሚመለከት በመሆኑና ከውጪ ያሚገቡትን መተካት የሚችል አማራጪ በሃገር ውስጥ ሳይኖር ለመተግበር ማሰቡን ማህበሩ ተገቢ እንዳልሆነ አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉዳዩ ላይ ከሰሞን በሰጡት ማብራሪያ መፍትሄው አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለውን ታክስ መቀነስ እንደሆነና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡት የተለየ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።