በአገር መከላከያ ሰራዊት የተፈጠረው ከፍተኛ አለመግባባት መንስኤዎች ይፋ ወጡ

በአገር መከላከያ ሰራዊት የተፈጠረው ከፍተኛ አለመግባባት መንስኤዎች ይፋ ወጡ (ቪዲዮውን ከታች ያገኙታል)

360 ሚድያ ላይ በመከላከያ ሰራዊት የአገርን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር እየተፈፀመ እንዳለ ጥልቅና በበቂ ሰነድ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰው ዘግቧል፡፡ መሰረታዊ የአገርን ደህንነት ሊጎዱ የሚችሉ መረጃዎችን ከመግለፅ የተቆጠበው ሚድያው በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ለተፈጠረው አለመግባባት ምክንያቶች ናቸው ያላቸውን ዘርዝሯል፡፡

ከምክንያቶቹ መካከል፡-

1. በአሁኑ ጊዜ በመከላከለያ ውስጥ በከፍተኛም ሆነ በመካከለኛ አመራር ውስጥ በጣም ከፍተኛ የሆነ አለመግባባትና ግብግብ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነው አንዱና መሰረታዊ ነገር የዓረቦች ጣልቃገብነት ነው፡፡ ጣልቃገብነቱ በመከላከያ ውስጥ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል፡፡ የመከላከያ አመራሮች ዓረቦች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እያሳዩት ያለው ጣልቃገብነት የአገሪቱ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡ ስለዚ ይሄ ነገር ሊታረም ይገቧል በሚል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸሟቸው ሌሎች የመከላከያ አመራሮችም ከፍተኛ ንትርክና ግብግብ ተፈጥሯል፡፡ የተወሰኑ ማሳያዎች ለመጥቀስ ያህል ጀነራል ሰዓረ መኮነን ከመገደላቸው ከ15 ቀናት በፊት ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ውሳኔ ላይ ተደርሶ የጀነራል ሰዓረን ቦታ በመተካት ስልጣን የሚይዘው ጀነራል አደም እንዲሆን ተወስኖ ነበር፡፡ ጀነራል አደምም ከደህንነት መስሪያቤት እንደሚነሳ ተነግሮት ኃላፊነቱን ሲያስረክብ ነበር፡፡ ሲጠየቅ ደግሞ ይል የነበረው “የሰዓረን ቦታ ልተካ ነው” የሚል ነበር፡፡ አንድ ግዜ አንስተነው የነበረው ጥያቄ ጀነራል ሰዓረ ከመሞታቸው ከ15 ቀናት በፊት ከስልጣናቸው ተነስተው ጀነራል አደም ይተካ ከነበረ ጀነራል ሰዓረ የሚነሱበት ምክንያት ምን ነበረ? ከስልጣን ከተነሱ በኋላስ ምንድነው የሚደረጉት? እንደተደረገው ተገድለው ነው ዞር የሚደረጉት ወይስ ሌላ የተዘጋጀላቸው ኃላፊነት አለ? የሚል ጥያቄ ነበር፡፡ አሁን ግዜው እየገፋ ስለመጣ አንዳንድ ምልክቶች ወደ አደባባይ መጥተዋል፡፡

2. አሁን ዓረቦች በተጨባጭ እያደረጉት ያሉት የመከላከያ ቤዝ ለመገንባት የገንዘብ ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ መዋቅሩ ድረስ ይሳተፋሉ፡፡ ልክ እንደ ፔንታጎን ሁሉንም ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው የመከላከያ ተቋም ለመገንባት ነው ያቀዱት፡፡ ስለዚህ እዛ የመገናኛ አውታሮች ሊዘረጉ ነው፤ የመሰለያ መዋቅሮች ሊዘረጉ ነው፤ የአገሪቱ ምስጢር የሚገኝበት ክፍል ሊገነባ ነው፡፡ ይህንን ስራ ዓረቦች ሙሉ ኃላፊነት ወስደው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተ-መንግስቱን ለማሳደስ በሚል እድል እንደሰጡዋቸው ሁሉ የመከላከያ ቤዝም ለዓረቦች ሊሰጡ ሲሉ ጀነራል ሰዓረ “ይሄ ነገር የአገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ነው፣ ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፣ የትም አለም የመከላከያ ቤዝ ለተለየ ብሄራዊ ጥቅም ላላቸው አገራት አይሰጥም፣ ይሄ ቁልፍ የሚስጥር ጉዳይ ነው፣ የአገሪቱ ህልውና ጉዳይ ነው” ብለው ጀነራል ሰዓረ ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡ ከዛ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሰጡት ትእዛዝ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ ጀነራል ሰዓረ “ከኃላፊነቴን ለቅቄ ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ወድቃለች ብየ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናገራለሁ” የሚል አቋም ይይዛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ይህንን ነገር በጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለማስፈፀም ሞክረው ግብግቡ ሲጠናከር ነገር እንዲቆም ተደረገ፡፡ ይሄ ነገር ቆሞ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በተገደሉበት ጊዜ ጀነራል ሰዓረም ተገደሉ፡፡.