የኢራንና የዩናይትድ ስቴትስ የጠላትነት ቁንፅል ወግ

ክሮከር ጄኔቭ ዉስጥ የኢራኑ ወጣት ጄኔራል ቃሲም ሱሌይማኒይ ከላኳቸዉ የቴሕራን ባለስልጣናት ጋር የአፍቃኒስታኑን አክራሪ ገዢ ፓርቲ ታሊባንን እና አልቃኢዳን በጋራ ለማጥፋት ተስማምተዉ ተመለሱ።የአሜሪካ ጦር በጄኔራል ሱሌማንይ ትዕዛዝ ከኢራን በሚንቆረቆርለት መረጃ እየታገዘ የአልቃኢዳና የታሊባን ስልታዊ ይዞታዎችን ያወድመዉ ያዘ።…