የጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ ተብሎ የኦፌኮ ፓርቲ መታወቂያ ማግኘቱ ከሕግ አንፃር አነጋጋሪ ሆኗል።

የጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ ተብሎ የኦፌኮ ፓርቲ መታወቂያ ማግኘቱ ከሕግ አንፃር አነጋጋሪ ሆኗል።ማሕበራዊ ሚዲያው የሕግ አግባብን የተከተለ አይደለም በማለት እየተነጋገረበት ይገኛል።

ጦማሪ ስዩም ተሾመ የሚከተለውን ጽፏል።

Image may contain: 1 personጃዋር መሃመድ የተጭበረበረ መታወቂያ አወጣ “የቆጡን አወርድ ብሎ የብብቷን ጣለ”

ምክንያቱም አቶ ጃዋር የአሜሪካ ዜግነቱን ሳይመልስ መታወቂያው ላይ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ተገልጿል።

አንደኛ፦ ትክክለኛውን የህግ አግባብ በተከተለ መልኩ የነዋሪነት መታወቂያ የሌለው ግለሰብ ራሱን “ኢትዮጵያዊ” ብሎ የአባልነት መታወቂያ ማውጣት አይችልም።

ሁለተኛ፦ የአሜሪካ ዜግነቱን ለመመለስ በቅድሚያ ከOMN ጋር በተያያዘ የተጀመረው የታክስ ማጭበርበር ወንጀል ምርመራ መጠናቀቅ አለበት።

አቶ ጃዋር ባለፈው ወደ አሜሪካ የሄደው በOMN ስም በFundraising አማካኝነት የሰበሰበውን ወደ 300ሺህ ዶላር ለማስለቀቅ ነበር። ነገር ግን የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ገቢ መስሪያ ቤት በOMN ላይ ምርመራ መጀመሩን ሲያውቅ ተስፋ ቆርጦ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ። ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ጃዋር አሜሪካ ውስጥ በፌስቡክ አማካኝነት ለራሱ ሆነ ለOMN ገንዘብ መሰብሰብ አይችልም።

ስለዚህ እንደ አዲስ የገንዘብ መሰብሰቢያ ያደረገው ኦፌኮን ነው። የኦፌኮ አባል ለመሆን ደግሞ እንደለመደው የአሜሪካን ዜግነት ጥሎ የአባልነት መታወቂያ አወጣ። ይሁን እንጂ ጃዋር የኢትዮጵያ ዜግነት ለማግኘት በቅድሚያ የአሜሪካን ዜግነት መታወቂያ በህጉ አግባብ መመለስ አለቀት። የአሜሪካን ዜግነት በአግባቡ ለመመለስ ደግሞ በቅድሚያ የሀገሪቱ መስሪያ ቤት የጀመረው ምርመራ መጠናቀቅ አለበት።

ምርመራው ሲጠናቀቅ ደግሞ ጃዋር የOMN ስራ አስኪያጅ ከሆነበት 2015 ጀምሮ ለፈፀመው የታክስ ማጭበርበር መጠየቅ አለበት። በአሜሪካ መንግስት የተጀመረውን ምርመራ ለማምለጥ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በተጨብረበረ መንገድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለማግኘት በመሞከሩ ደግሞ በኢትዮጵያና አሜሪካን መንግስት ተፈላጊ ወንጀለኛ ያደርገዋል። “የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች!” ይሉሃል!!