የአሜሪካን ዜግነቴን ለመመለስ በሒደት ላይ ነኝ – ጀዋር መሐመድ ( ለDW በሰጠው ቃለ ምልልስ) ቃለምልልሱን ያድምጡ።

DW : የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ እና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ OMN ዋና ሃላፊ አቶ ጀዋር መሐመድ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ በምህጻሩ ኦፌኮን በአባልነት መቀላቀላቸውን አስታወቁ። አቶ ጀዋር ዛሬ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአሜሪካን ዜግነታቸውን ለመመለስ በሂደት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊነታቸውን እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ፓርቲን ስለመቀላቀልዎ መረጃዎች እያመለከቱ ነው ምን ያኽል እውነት ነው? የተባሉት አቶ ጀዋር መልሳቸው፤ «እውነት ነው።» የሚል ነው።
ያነጋገራቸው ታምራት ዲንሳ ነው። ቃለምልልሱን ያድምጡ።